ቀጥታ፡

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለት ሳምንት ጨዋታዎች ማስተካከያ ተደረገባቸው

አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 20/2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ እና 17ኛ ሳምንት መርሐግብር ማሻሻያ እንደተደረበት የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።
የፕሪሚየር ሊጉ ከ14ኛ እስከ 17ኛ ሳምንት በድሬዳዋ ስታዲየም ለማካሄድ መርሐግብር ወጥቶ በመከናወን ላይ ይገኛል።

በ15ኛው ሳምንት የሶስተኛ ቀን ጨዋታ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ ዝናብ ጨዋታዎች ተቋርጠው ነገ እና ከነገ በስቲያ እንዲካሄዱ መወሰኑ ይታወቃል።

የ15ኛው ሳምንት የቀን ለውጥ የተደረገባቸውን ጨዋታዎችን ተከትሎ የቀጣይ 16ኛ እና 17ኛ ሳምንት መርሐግብሮችን ለማስተካከል በማስገደዱ ምክንያት ማሻሻያ መደረጉን ማህበሩ ገልጿል።

በዚሁ መሰረት የሁለቱ ሳምንት ጨዋታዎች ከየካቲት 23 እስከ መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም