ተራዝመው የነበሩ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
ተራዝመው የነበሩ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 20/2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተራዝመው የነበሩ የ15ኛ ሳምንት መርሐግብር አራት ጨዋታዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ይከናወናሉ።
በድሬዳዋ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ሜዳው ማጫወት ባለመቻሉ ትናንት እና ከትናንት በስቲያ መደረግ የነበረባቸው ጨዋታዎች መራዘማቸውን የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቆ ነበር።
አሁን በድሬዳዋ ባለው የተሻለ የአየር ጸባይ ምክንያት ጨዋታዎቹ ነገ እና ከነገ በስቲያ እንዲካሄዱ መወሰኑን የማህበሩ የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ገልጿል።
በዚሁ መሰረት ነገ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሲዳማ ቡና ከቀኑ 10 ሰአት (ከተቋረጠበት 18ኛ ደቂቃ የሚቀጥል) እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ ከምሽቱ 1 ሰአት በድሬዳዋ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ረቡዕ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከተማ ከቀኑ 10 ሰአት፤ ባህር ዳር ከተማ ከወላይታ ዲቻ ከምሽቱ 1 ሰአት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ከአራቱ ጨዋታች በኋላ የመጀመሪያው ዙር ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ዙር ውድድር ይጠናቀቃል።