ቀጥታ፡

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር የ15ኛ ሳምንት አራት ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘሙ

አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 19/2015 በድሬዳዋ ስታዲየም ሊካሄዱ የነበሩ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር የ15ኛ ሳምንት አራት ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ መራዘማቸው ተገለጸ።

ጨዋታዎቹ የተራዘሙት በድሬዳዋ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ስታዲየሙ ማጫወት አለመቻሉን የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ በማሳወቁ ምክንያት መሆኑን የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

በዚህም ምክንያት ዛሬ ሊደረጉ የነበሩት የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም የባህር ዳር ከተማ እና የወላይታ ዲቻን ጨምሮ ከትናንት መርሐግብሮች 18ኛው ደቂቃ ላይ የተቋረጠው የኢትዮ ኤሌትሪክ እና ሲዲማ ቡና እና ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታዎች ተራዝመዋል።

ጨዋታዎቹ የሚካሄድባቸው ቀናት በቀጣይ ይፋ እንደሚደረጉ አክሲዮን ማህበሩ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም