ቀጥታ፡

የሲዳማ ቡና እና የኢትዮ ኤሌትሪክ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በከባድ ዝናብ ምክንያት ተቋረጠ

አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 18/2015 ቤትኪግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሲዳማ ቡና በድሬዳዋ ስታዲየም እያደረጉት የነበረው ጨዋታ ከባድ ዝናብ ምክንያት ተቋርጧል።

በዝናቡ ምክንያት ድሬዳዋ ስታዲየም ማጫወት እንደማይችል የጨዋታ አመራሮች በማሳወቃቸው ጨዋታው በ18ኛው ደቂቃ ላይ መቋረጡን የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

ከምሽቱ 1 ሰአት በ15ኛ ሳምንት መርሐግብር ኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ የሚያደርጉት ጨዋታ የመካሄድ ጉዳይ ከቆይታዎች በኋላ ምላሽ እንደሚያገኝም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም