ቀጥታ፡

በፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኘ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 18/2015 በፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ የተመራ ከፍተኛ አመራሮች የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የስራ ጉብኝት አካሄደ።

ከፍተኛ አመራሮቹ በተቋሙ የመድኃኒት መከማቻ መጋዘን ( pharmaceutical warehouse)፣ እና የተለያዩ የስራ ክፍሎች ተዟዙረው ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ ስለ ተቋሙ የስራ እንቅስቃሴ ገለጻ አድርገዋል።

አመራሮች በዓለም አቀፍ ብሎም በኢትዮጵያ በተለያዩ ተግዳሮቶች በመፈተን ላይ ያለውን የአቅርቦት ሰንሰለት በመቋቋም ለማህበረሰቡ የመድኃኒት አቅርቦትን ለማሻሻል እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

የተቋሙን ስራ ውጤታማ እና ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ መዋቅር ማሻሻልና በፖሊሲ ማዕቀፍ መልስ የሚሹ ጉዳዮች ላይ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም