የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ በ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን መድኃኒት ቤት አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ በ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን መድኃኒት ቤት አስመረቀ
ሻሸመኔ (ኢዜአ) የካቲት 17/2015 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ በ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን መድኃኒት ቤት አስመረቀ።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምዕራብ አርሲ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከማል አብደላ እንደተናገሩት መድኃኒት ቤቱ ለ400 ሺህ ሰዎች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው።
ማህበሩ በዞኑ በተለያዮ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ሰብአዊ ድጋፎችን ከማድረግ ጎን ለጎን የሕዝቡን ጤና የሚያሻሽሉ መሰረተ ልማቶችንም እየገነባ ይገኛል ብለዋል።
ከመሰረተ ልማቶቹ መካከል በዞኑ ዶዶላ ከተማ በ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ግንባታው የተከናወነው መድኃኒት ቤት ለአገልግሎት በቅቷል ነው ያሉት።
ማህበሩ በዞኑ 5 ቅርንጫፎች እንዳለው ገልጸው በቅርንጫፎቹ አማካኝነት በስድስት ወራት ውስጥ 200 ሺህ ለሚሆን የዞኑ ሕዝብ የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት መስጠቱንም ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በ3 ሚሊዮን ብር የተለያዩ መስረተ ልማቶችን እያስገነባ ሲሆን 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ በተለያዩ ምክንያት ለችግር ለተዳረጉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።
የምዕራብ አርሲ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አስፋ ቶለሳ በበኩላቸው ማህበሩ በዞኑ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የዞኑ ህዝብም በማህበሩ በኩል የተገነቡ መሰረት ልማቶችን በአግባቡ መጠቀምና መጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል።