ቀጥታ፡

የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የአድዋ ድል መታሰቢያ "የአድዋ ዜሮ ሙዚየም" ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 17/2015 የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የአድዋ ድል መታሰቢያ "የአድዋ ዜሮ ሙዚየም" ፕሮጀክትን ጎበኙ ፡፡

በ3 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው እና ባለ አምስት ወለሉ ፕሮጀክት የአድዋን ድል፣ የኢትዮጵያውያንን ጀግኖች፣ የአድዋን መልክዓምድር በሚወክል መልኩ እየተገነባ ይገኛል።

ሙዚየሙ በአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር መነሻ የተሰየመው የአንድነት መነሻ ማዕከል ተደርጎ በመቆጠሩ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን በጥቅምት 2016 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የአድዋ ጦርነት እና የድል ክፍለ ታሪክን ከቦታ ጋር አዛምዶ መያዙም እና የአድዋን ሰንሰለታማ ተራሮች፣ የፈረሰኞች ፣ ለሴት ጀግኖች ክብር የተሰየመ ማስታወሻ፣ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነፃነት ማስታወሻ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጀግኖች ጉዞና 5 የመግቢያ በሮች እንዳሉት ተመላክቷል።

በውስጡም የከተማ አስተዳደሩ ምክርቤት አዳራሽን ጭምሮ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችን የሚያስተናግድ አዳራሽ1 ሺህ መኪኖችን የሚያስተናግድ ፓርኪንግ፣ የመዝናኛ ሥፍራዎች የስፖርት ማዘውተሪያዎች ሲኒማ እና የኤግዚቢሽን አገልግሎትን ያካተተ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም