በፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ እና ሐዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ እና ሐዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል
አዲስ አበባ(ኢዜአ) የካቲት 16/2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐግብር የመጀመሪያ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ እና ሐዋሳ ከተማ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።
በድሬዳዋ ስታዲየም ዛሬ በተደረገው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ተመስገን ደረሰ በስምንተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ አርባ ምንጭ ከተማን መሪ ማድረግ ችሎ ነበር።
በ20ኛው ደቂቃ ሐዋሳ ከተማ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ሙጂብ ቃሲም ወደ ግብ በመቀየር ቡድኑን አቻ አድርጓል።
በተያያዘም በ15ኛ ሳምንት መርሐግብር በአሁኑ ሰአት በድሬዳዋ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ ጨዋታቸውን እያደረጉ ሲሆን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰአት ምንም ግብ አልተቆጠረም።