የኢትዮጵያ መንግስት በጄኔቫ ከሚገኙ የባለ ብዙ ወገን ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ መንግስት በጄኔቫ ከሚገኙ የባለ ብዙ ወገን ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 16/2015 የኢትዮጵያ መንግስት በጄኔቫ ከሚገኙ ዓለም አቀፍ የባለ ብዙ ወገን ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጄኔቫ ቢሮ እና በስዊዘርላንድ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው በጄኔቫ የተመድ ቢሮ ዳይሬክተር ጀነራል ታቲያና ቫሎቫያ የሹመት ደብዳቤያቸውን አስገብተዋል።
አምባሳደር ፀጋአብ ከዳይሬክተር ጀነራሏ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና ለውጦች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል።
አምባሳደሩ የኢትዮጵያ መንግስት በጄኔቫ ከሚገኙ ዓለም አቀፍ የባለ ብዙ ወገን ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን አመላክተዋል።