ቀጥታ፡

“የኢትዮጵያ እና የቻይና ማዕከላዊ ባንኮችን ትብብር ማስፋት የሚያስችል ትልቅ አቅም አለ”--የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዥ ማሞ ምህረቱ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 16/2015 “የኢትዮጵያ እና የቻይና ማዕከላዊ ባንኮችን ትብብር ማስፋት የሚያስችል ትልቅ አቅም አለ”ሲሉ የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ማሞ ምህረቱ ከቻይና ማዕከላዊ ባንክ ዳይሬክተር ጄኔራል ይ ጋንግ ጋር በቤጂንግ ተወያይተዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያ እና ቻይና የሁለትዮሽ ግንኙነት ጠንካራ የኢኮኖሚ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን አቶ ማሞ ምህረቱ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም