ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ከቻይና ንግድ ሚኒስቴር የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጄንሲ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ከቻይና ንግድ ሚኒስቴር የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጄንሲ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 15/2015 የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ከቻይና ንግድ ሚኒስቴር የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጄንሲ ዳይሬክተር ሊዩ ዲያንክሰን ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም በተቋማቱ መካከል ያለውን ትብብር በኢንቨስትመንት አጋርነት እና በኢንቨስትመንት ማስፋፋት ዘርፍ ለማጠናከር መስማማታቸውን በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ቡድን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከትናንት በስቲያ ቻይና መግባቱ ይታወሳል።
ልዑኩ በቆይታው ከቻይና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋል።