ቀጥታ፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዓለም ምርጥ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 14 ቀን 2015 በዘንድሮው ዓመት የተካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዓለም ምርጥ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አሸናፊ ሆነ።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት "የአለም ምርጥ 10 ኪሎ ሜትር" የጎዳና ላይ ሩጫ ምርጥ ተብሏል።

 በአንድነት የተቀመጠው በአትሌቲክስ አንቱ የተባሉ ባለሙያዎች በሚያዘጋጁት ራነርስ ዎርልድ በተባለው መጽሄት ነው። 

በዘንድሮው ዓመት የተካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር በራነርስ ወርልድ የቀዳሚነት ደረጃን ሲያገኝ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ነው።

 ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በመቀጠል በዘንድሮው ዓመት ምርጥ የጎዳና ላይ 10 ኪሎሜ ትር ሩጫ ቀጥሎ የለንደኑ ቪታሊቲ 10 ሺህ ሜትር ሁለተኛ ደረጃን አግኘቷል። 

የፓሪስ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ደግሞ የሶስተኛ ደረጃን ይዟል። 

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2019 ዘ ቻለንጅ አዋርድ በሚያዘጋጀው ዓመታዊ የሽልማት ውድድር በጎዳና ላይ ሩጫ ዝግጅት ዘርፍ በአለም ቀዳሚ ሆኖ መመረጡም ይታወሳል። 

ለዚህ መሳካትና ኢትዮጵያን በበጎ እንድትነሳ ገጽታ ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅ እያደረጉ ያሉትን ባለድርሻ አካላትና መላው ኢትዮጵያዊን ታላቁ ሩጫ በኢትጵያ ምስጋናውን አቅርቧል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም