ቀጥታ፡

ቻይና የኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ፈቀደች

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 14/2015 ቻይና የኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ፍቃድ ሰጠች።

ውሳኔው ከየካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ አመልክተዋል።

ፈቃዱ ቻይና በቅርቡ ይፋ ባደረገችው “ የአፍሪካ ልዩ ቀረጥ ማሻሻያ” ማዕቀፍ ስር እንደሚተገበርና 98 በመቶ የኢትዮጵያ ምርቶች ላይ ቀረጥ እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል።

በዚሁ መሰረት 8 ሺህ 804 የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ ቻይና ከቀረጥ ነጻ እንደሚገቡ ተናግረዋል።

“ይህ የተሻለ የተጠቃሚነት አማራጭ ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች መጠን ያሳድጋል” ብለዋል።

ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብዙ ጠቀሜታዎችን ይዞ ይመጣል ያሉት አምባሳደሩ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ወዳጅነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም