ቀጥታ፡

በ44ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ስፖርት ልኡክ ወደ ሀገሩ ተመልሷል

የካቲት 14/2015/ኢዜአ/ በ44ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አውስትራሊያ ባትረስት ከተማ ሰሞኑን በተካሄደው ውድድር ላይ በ2 ወርቅ፣ በ7 ብር፣ በ1 ነሃስ በድምሩ በ10 ሜዳልያዎች ከአለም ሃገራት 2ኛ ደረጃን የያዘው የኢትዮጵያ ስፖርት ልኡካን ቡድን ወደ ሀገሩ መመለሱን የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

የስፖርት ልኡካኑ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገውለታል።

አምባሳደር መስፍን አትሌቶቹ ላስመዘገቡት ድል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ለስፖርት ልኡካን ቡድኑ ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ላይ በስካይ ላይት ሆቴል የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት መርሃ ግብር እንደሚካሄድም ፌዴሬሽኑ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም