ኢትዮጵያና አቡዳቢ በመከላከያ ኢንዱስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት መሥኮች በጋራ ለመሥራት ተሥማሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያና አቡዳቢ በመከላከያ ኢንዱስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት መሥኮች በጋራ ለመሥራት ተሥማሙ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 13/2015 ኢትዮጵያና አቡዳቢ በመከላከያ ኢንዱስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት መሥኮች በጋራ ለመሥራት ተሥማሙ።
በመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይና በመከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ የተመራ ልዑክ የመከላከያ አለም አቀፍ ኤግዚቪሽንና ኮንፈረንስ ላይ ለመሳተፍ አቡዳቢ ገብቷል::
በቆይታቸው ከተባበሩት አረብ ኢምሬት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ከመከላከያ ሚኒስትሩና ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጋር በመገናኘት በሁለቱ ሀገራት መካከል እስከ አሁን የነበሩ አጠቃላይ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር እና ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ መክረዋል፡፡
የኢትዮጵያ እና የአቡዳቢ ወዳጅነትና ትብብር የቆየ ቢሆንም ይህንኑ በጎ ገፅታ ለማሥቀጠል በቀጣይ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ዘርፎችም ተወያይተዋል፡፡
የመከላከያ ኢንደስትሪ የልማትና ኢንቨስትመንት ስራዎች በተቋሙም ሆነ በሀገር ላይ ያለውን ዘላቂ ጠቀሜታ በመገንዘብ በእነኝህ ዘርፎች የመልካም ተሞክሮ ልውውጥ ከማድረግ ባለፈ ይበልጥ ማሥፋት በሚቻልባቸው መንገዶች በዝርዝር ተወያይተዋል::