ቀጥታ፡

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአፍሪካ ሀገራት ቀዳማዊት እመቤቶች አቀባበል አደረጉ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 11/ 2015 ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአፍሪካ ሀገራት ቀዳማዊት እመቤቶች በቤተ መንግስት አቀባበል አደረጉ ።

አቀባበል የተደረገላቸው የ12 የአፍሪካ ሀገራት ቀዳማዊት እመቤቶች እና ልዑካቸው በ27ኛው መደበኛ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ተቋም አጠቃላይ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተሳተፉ ያሉ ናቸው፡፡

May be an image of 5 people, child, people standing and indoor

በአቀባበል ሥነ ስርዓቱ ላይ የተለያዩ ባህላዊ የኢትዮጵያ ምርቶች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

ሀገር በቀል ምርቶቹን ከማስተዋወቅ አንጻርም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

ጉባዔው ከየካቲት 8 ቀን 2015 ጀምሮ በስርዓተ ጾታ እኩልነት የሚታየውን ክፍተት መዝጋት በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ መሆኑን የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም