የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችንና አዋጆችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችንና አዋጆችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

አዳማ፣ የካቲት 11 ቀን 2015 (ኢዜአ) የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የስራ ዘመን 2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችንና አዋጆችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

በዚህም መሰረት አቶ መስፍን መላኩ በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የኦሮሚያ ከተሞች ክላስተር አስተባባሪ፣
አቶ ከፍያለው ተፈራ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሰላምና ፀጥታ ክላስተር አስተባባሪ፣
አቶ አህመድ ኢንድሪስ የኦሮሚያ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ፣
አቶ ጌቱ ገመቹ የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ሃላፊ፣
አቶ ሁሴን ፈይሶ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ፣
አቶ ጉዮ ዋሪዮ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣
ወይዘሮ ኮኮቤ ዲዳ የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ፣
አቶ ሙሐመድ ጉዬ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ሃላፊ፣
አቶ ዳንኤል ቸርነት የንግድ ቢሮ ሃላፊ፣
አቶ ማቲያስ ሰቦቃ የስራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ፣
ኢንጂነር ግርማ ረጋሳ የመስኖና አርብቶ አደር ቢሮ ሃላፊ፣
ዶክተር አደሬ አሰፋ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች ሃላፊ፣
አቶ በድሪ ዑመር የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት፣
አቶ ገልማ ዋቆ በጨፌ ኦሮሚያ የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።
ጨፌው በተጨማሪም የኦሮሚያ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲሁም የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት አዋጆችን በማፅደቅ ተጠናቋል።