አየር መንገዱ በተርኪዬ የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሰብአዊ አቅርቦት የማድረስ ተግባርን ተቀላቀለ - ኢዜአ አማርኛ
አየር መንገዱ በተርኪዬ የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሰብአዊ አቅርቦት የማድረስ ተግባርን ተቀላቀለ
የካቲት 10/2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተርኪዬ የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሰብአዊ አቅርቦት የማድረስ ተግባር መቀላቀሉን ገለጸ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትዊተር ገጹ ባወጣው መረጃ እጅግ አስከፊ በሆነው የተርኪዬ መሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ የማጓጓዙን ተግባር መቀላቀሉን ገልጿል።
በዚህም አየር መንገዱ በእቃ ጫኝ አውሮፕላኖቹ ከሜክሲኮ መንግስት ለተርኪዬ የተለገሰ 100 ቶን የሰብአዊ አቅርቦት ማጓጓዙን አስታውቋል።
በቱርክዬና ሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ40ሺህ በላይ ሰዎች ለሕልፈተ ሕይዋት መዳረጋቸው ተዘግቧል።