ቀጥታ፡

የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርቻንጄ ቶውድራ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 10/2015 በ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርቻንጄ ቶውድራ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምናልባት የ3 ሰዎች፤ የቆሙ ሰዎች እና የቤት ውስጥ ምስል

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ የቻድ፣ የኬኒያ፣ የሞሪታኒያ፣ የኬፕቬርዴ እና የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

“የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ከነገ ቅዳሜ የካቲት 11/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ የሚካሄድ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም