ቀጥታ፡

የቻድ ፕሬዝዳንት መሃማት ዲቤይ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 10/2015 “የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው 36ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የቻድ ፕሬዝዳንት መሃማት ኢድሪስ ዲቤይ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምናልባት የ5 ሰዎች እና የቆሙ ሰዎች ምስል

ፕሬዚደንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ናሲሴ ጫሊና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ሌሎ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የኬኒያ ፣ የሞሪታኒያ፣ የኬፕቬርዴ፣ የሞዛምቢክ፣ የሴራሊዮን፣ የኮሞሮስ፣ የቡሩንዲ፣ የታንዛኒያ፣ የሩዋንዳ፣ የሌሴቶ፣ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንቶች ጨምሮ የሌሎች አገራት መሪዎች ገብተዋል።

ምናልባት የ3 ሰዎች፤ የቆሙ ሰዎች እና ከቤት ውጪ ምስል

እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የዑጋንዳ እና የደቡብ ሱዳንና የሊቢያ ምክትል ፕሬዚዳቶች እና የሌሎች የአፍሪካ አገራት መሪዎችም መዲናዋ ገብተዋል።

“የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ከነገ የካቲት 11 ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት አዲስ አበባ ከተማ በአፍሪካ ሕብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም