ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ 185 የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ሥራ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ 185 የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ሥራ ገቡ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 9/2015 የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የገዛቸውን 185 የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ሥራ ማስገባቱን አስታወቀ።
ድርጅቱ መኪኖቹን ወደ ሥራ የማስገባትና የማስመረቅ መርሐ ግብሩን ዛሬ በሞጆ ደረቅ ወደብና ተርሚናል አከናውኗል።
በሥራ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።