ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት ተፈታ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8/2015 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በውይይት መፈታቱ ተገለጸ፡፡

በቤተ ክርስቲያኒቱ የገጠመውን ፈተና ለመፍታት የሁለቱ ወገኖች የሐይማኖት አባቶች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ ምክክር አድርገዋል፡፡

አንድነትን የሚያጸና እናአገልግሎትን የሚያሰፋ መንገድ መከተል ተገቢ መሆኑን በማመን ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን የሐይማኖት አባቶች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

May be an image of 6 people

ከቋንቋ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ቤተ ክርስቲያን የጀመረችውን ሥራ አጠናክራ እንደምትቀጥል ከመግባባት ላይ መደረሱ ተመላክቷል፡፡

ለዚህም በጀትና የሰው ኃይል ማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶት ይሠራል ነው የተባለው፡፡

May be an image of 3 people and beard

በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ እምነትን ማጠናከር የሚያስችሉ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲጠናከሩ እና ቤተ እምነቱን ለትውልድ ለማሻገር መፈታት ያለባቸው ሥራዎችን ለማከናወን መግባባት ላይ እንደተደረሰ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም