የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ የልማት ተግባራት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ የልማት ተግባራት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 7/2015 የኢትዮጵያን እድገት ለማፋጠን መንግስት የሚያከናውናቸውን የልማት ተግባራት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ እንደሚደግፍ የአለም ባንክ አስታወቀ።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከአለም ባንክ የልዑካን ቡድን አባላትጋር የተወያዩ ሲሆን በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ተግባራትን በመለየት በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል።
ዓለም ባንክ የኢትዮጵያን ልማት በማገዝና በመደገፍ ከፍተኛ ሚና ያለዉ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሯ ድጋፉ በጋራ የልማት ስራዎችን በመተግበር እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን በበኩላቸው ባንኩ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያን እድገት ለማፋጠን መንግስት የሚያከናውናቸውን የልማት ተግባራት እየደገፈ መቆየቱን ተናግረዋል።
የድጋፍ ተግባራቱን አሁንም አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።