በ42ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል - ኢዜአ አማርኛ
በ42ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 7/2015 በ42ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
በየአገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተመራው ልዑካን ቡድን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
እስካሁንም የሶማሊያ፣ የሴራሊዮን፣ የናይጄሪያ፣ የኮትዲቭዋር፣ ታንዛኒያ፣ ማሊ፣ ዚምባብዌ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኢስዋቲኒ፣ ኮሞሮስ እና የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ልዑካን ቡድኖቻቸው አዲስ አበባ ገብተዋል።
በአስፈፃሚ ምክር ቤት በስብሰባ ላይ የሚሳተፉ የሌሎች አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የልዑካን ቡድኖቻቸው አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ይሆናል።
በህብረቱ ጉባዔ የአየር ንብረት ለውጥ ተጠቂነትን በመቀነስ አገራት የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እያጋጠሟቸው ያሉ ፈተናዎችን መሻገር የሚያስችሉ ምክረ ሃሳቦች ይንሸራሸራሉ ተብሎ ይጠበቃል።