50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ትምህርት ለመከታተል የሚያስችላቸው የአቅም ማሻሻያ ነጥብ ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ትምህርት ለመከታተል የሚያስችላቸው የአቅም ማሻሻያ ነጥብ ይፋ ሆነ
የካቲት 06/2015(ኢዜአ) በ2014 ትምህርት ዘመን 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎችና በተለያዩ አማራጮች ትምህርት ለመከታተል የሚያስችላቸው የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ይፋ ተደረገ።
የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።
በዚሁ መሠረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።
- በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።
- ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።