ቀጥታ፡

ተጠባቂው የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 4/2015 በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ያደረጉት ጨዋታ በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተከናወነው ጨዋታ መሐመድ ኑር ናስር በ43ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ ቡናን መሪ ቢያደርግም የቅዱስ ጊዮርጊሱ የክንፍ መስመር ተጫዋች ቸርነት ጉግሳ በ73ኛው ደቂቃ ግብ በማስቆጠር ቅዱስ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል።

የአቻ ውጤቱን ተከትሎ ፈረሰኞቹ ነጥባቸውን ወደ 26 ነጥብ ከፍ በማድረግ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር በነጥብ እኩል በመሆን እና በግብ ክፍያ በመብለጥ መሪነቱን ተረክበዋል።

በአንጻሩ ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን ወደ 18 በማሳደግ ከነበረበት ዘጠነኛ ወደ ስምንተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም