የህብረት ስራ ማህበራትን ማጠናከር ህብረተሰብን መደገፍ ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

203

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 2/2015 የህብረት ስራ ማህበራትን ማጠናከር ህብረተሰብን መደገፍ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ሁለተኛው ከተማ አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት ኤግዚቢሽንና ሲምፖዚየም በኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ ተጀምሯል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ፍትሃዊ የግብይት ስርዓት እንዲኖር በማድረግ ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነት ጫናን በማቃለል፣ ለህብረተሰቡ ምርትንና ሸቀጥን በየአካባቢው በእሁድ ገበያ እና በሸማች ሱቆች በኩል ተደራሽ በማድረግ ረገድ የህብረት ስራ ማህበራት የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች “ሁላችንም አብሮነታችንን በማጠናከር ለህዝባችን ኑሮውን የሚያቃልል ስራ እንጂ የሚያከብድ ተግባር ላይ እንዳንሰማራ አደራ ለማለት እወዳለሁ” ማለታቸውን ከማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም