31ኛው የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የፖሊሲ አውጪ ሙያተኞች መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

የካቲት 2/2015 (ኢዜአ) 31ኛው የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የፖሊሲ አውጪ ሙያተኞች መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

መደበኛ ስብሰባውም ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት አምስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ተመላክቷል።

May be an image of 9 people and people standing

በዚህም የኢፌደሪ የአገር መከላከያ ሰራዊት የመከላከያ ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮንን በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አባል አገራት ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የቀጠናውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በሚል አስር አገራትን በአባልነት የያዘ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም