ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ

36

የካቲት 2/2015(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን የጋራ ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በቤኔሉክስ አገራት (ቤልጂየም፣ኔዘርላንድስ እና ሉክሰምበርግ) እና በአውሮፓ ሕብረት ተቋማት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከሕብረቱ የሰብአዊ መብቶች ልዩ ተወካይ ኢሞን ጊልሞር ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ሂሩት ለልዩ ተወካዩ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በተለያዩ አቅጣጫዎች ስለታዩ ለውጦች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

May be an image of text

የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ምላሽ አሰጣጥ እና በሽግግር ፍትሕ ስርዓት ውስጥ ተጠያቂነትን ማስፈንን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይም ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

ሁለቱ ወገኖች በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን የጋራ ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም