ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 1/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላለፉት ሁለት ቀናት በአውሮፓ ጣሊያን፣ ማልታና ፈረንሳይ ስኬታማ ጉብኝት አድርገው ዛሬ ማለዳ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው ይታወቃል።
በጉብኝታቸውም ከሀገራቱ መሪዎች ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፋዊ የትብብር መስኮች የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው የሚታወቅ ነው።