ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጅዳ የሚያደርገውን ዕለታዊ በረራ ወደ ሁለት ከፍ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 1/2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ጅዳ የሚያደርገውን መደበኛ ዕለታዊ በረራ ወደ ሁለት እንደሚያሳድግ አስታወቀ።

አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ ተጨማሪ በረራ ማድረግ የሚጀምረው የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም