የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌና ዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች አገልግሎት መስጠት ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌና ዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች አገልግሎት መስጠት ጀመረ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 30/2015 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌና ዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።
ዛሬ ከማለዳ አንስቶ 31 የባንኩ ቅርንጫፎች ስራ መጀመራቸውን የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።
ከሰዓት በኋላም ተጨማሪ 16 ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ አመልክተዋል።
የባንኩ ፕሬዝዳንት አገልግሎቱ እንዲጀመር አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።