በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው የሕዝበ-ውሳኔ ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ ተደርጓል-ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

183

አርባ ምንጭ (ኢዜአ) ጥር 30/2015 በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው የሕዝበ-ውሳኔ ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ውሳኔ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና አስተባባሪ ወይዘሪት መቅደስ መኮንን ለኢዜአ እንዳሉት የድምፅ ቆጠራው ትናንት ማታ ተጠናቆ አድራል።

ጊዜያዊ ውጤቱም የድምጽ አሰጣጥ በተካሄደባቸው በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺህ 771 ምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ጠዋት ተለጥፎ ህዝብ እየተመለከተ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ህዝብ ውሳኔ በክልሉ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦና  ጎፋ ዞኖች እንዲሁም  ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች ትናንት መካሄዱን አስታውሰዋል።

በየደረጃው የተሰማሩ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ታዛቢዎችና የጸጥታ አካላት የምርጫውን ስነ-ስርዓት ለማስፈጸም በተቀናጀ መንገድ መንቀሳቀሳቸውንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም