የክልል እና የዞን አመራሮች በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በመገኘት ድምጽ ሰጡ - ኢዜአ አማርኛ
የክልል እና የዞን አመራሮች በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በመገኘት ድምጽ ሰጡ

ጎፋ (ኢዜአ) ጥር 29/2015 የክልል እና የዞን አመራሮች በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት በስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ህዝበ ውሳኔ እያካሄደ ነው፡፡
በህዝበ ውሳኔው ድምጽ ከሰጡት የክልል እና የዞን የስራ አመራሮች መካከል የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ዶክተር ጌትነት በጋሻው፣ የደቡብ ክልል የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ እንዲሁም የደቡብ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር አክሊሉ አዳኝ ይገኙበታል።
በህዝበ ውሳኔው ላይ ለመሳተፍ በአጠቃላይ ከሶስት ሚሊዮን በላይ መራጮች ካርድ መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ የተገኙ የክልል እና የዞን አመራሮች በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል፡፡
ድምጽ ከሰጡት መካከል የጎፋ ዞን አስተዳደሪ ዶክተር ጌትነት በጋሻው አንዱ ሲሆኑ በዞናችን ከአደረጃጀት ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል ብለዋል፡፡
ህዝበ ውሳኔ የሚሰጥበት ምርጫ መካሄዱ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በበኩላቸው ምርጫው ዲሞክራሲን ለመገንባት ወሳኝ ድርሻ አለው ነው ያሉት፡፡

የደቡብ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ እንደተናገሩት ህዝቡ በቀጥታ የሚሳተፍበት ህዝበ ውሳኔ የዲሞክራሲ መገለጫና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡ይውደዱአስተያየትያጋሩ