በተርኪዬ በመሬት መንቀጥቀጥ ለደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ

2283

አዲስ አበባ ኢዜአ ጥር 29/2015፦በደቡባዊ ተርኪዬ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት መውደም የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስቴሩ በሀዘን መግለጫው በአደጋው ህይወታቸውን ስላጡት ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፤ ጉዳት የደረሰባቸውም በቶሎ እንዲያገግሙ የመልካም ምኞት መልዕክቱን አስተላልፏል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ከቱርኪዬ መንግሥት እና ህዝብ ጎን የምትቆም መሆኗን መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም