ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የሚኒስትሮች ልዑክ ቡድን በጣሊያን የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የሚኒስትሮች ልዑክ ቡድን በጣሊያን የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ ኢዜአ ጥር 29/2015፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሚኒስትሮች ልዑክ ቡድን በሮም፤ ጣሊያን የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ከፕሬዝዳንት ሴርጂዮ ማታሬላ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል ስላለው ግንኙነት እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።