ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮማሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በአርባ ምንጭ የድምጽ አሰጣጥ ሂደትን ታዘቡ

አርባ ምንጭ ጥር 29 ቀን 2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮማሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በአርባ ምንጭ በአሸም ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ታዝበዋል።

ኮማሽነር ዶክተር ዳንኤል የሚተዳደሩበት የክልል አደረጃጀትን ለመወሰን በደቡብ ክልል እየተደረገ ባለው የህዝብ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ከማለዳው ጀምሮ ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ በመካሄድ ላይ መሆኑ ገልጸዋል።

የድምጽ አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ዛሬ ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ያለው በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺህ 771 ምርጫ ጣቢያዎች መሆኑን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል።

በሕዝበ ውሳኔው ላይ 5 ሺህ 274 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች እንደሚሰማሩ ቀደም ሲል መግለጹም ይታወቃል።

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በአርባ ምንጭ በአሸም የምርጫ ጣቢያ በመገኘት የድምጽ አሰጣጠ ሂደቱን ታዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም