የጎፋ ዞን ነዋሪዎች የሚተዳደሩበትን ክልል ለመወሰን ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ እየሰጡ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የጎፋ ዞን ነዋሪዎች የሚተዳደሩበትን ክልል ለመወሰን ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ እየሰጡ ነው
ጥር 29/2015 (ኢዜአ) የሚተዳደሩበትን ክልል ለመወሰን የጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ነዋሪዎች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ እየሰጡ ነው፡፡
ድምጽ ሰጪዎች ከማለዳው ጀምሮ ሰልፍ በመያዝ ድምጽ እየሰጡ ሲሆን ምርጫ አስፈጻሚ ዎችና ታዛቢዎችም ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ላይ ተገኝተዋል።
ድምጽ አሰጣጡ ሰላማዊ በሆነ ድባብ ውስጥ እየተካሄደ መሆኑን ለመታዘብ ተችሏል።
በጎፋ ዞን ድምጽ ለመስጠት ከ304 ሺህ በላይ ዜጎች የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዞን ደረጃ ከ1 ሺህ 645 በላይ ምርጫ አስፈጻሚዎች አስፈላጊውን ስልጠና ወስደው የተሰማሩ ሲሆን ከተለያዩ ሲቪክ ተቋማት
የተወከሉ ምርጫ ታዛቢዎችም ተሰማርተዋል።
በአሁኑ ወቅትም ምርጫ ቦርድ በስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ሕዝበ ውሳኔ በማካሄድ ላይይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ በፊት ሲዳማና እና ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ ማካሄዱ የሚታወስ ነው።