የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ ዓመቱ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ ዓመቱ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አገኘ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 25/2015 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ ዓመቱ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱን የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ገለጹ።
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 37 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል።
ባንኩ በግማሽ ዓመቱ 13 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ገልጸው ይህም ከዕቅዱ ከመቶ በላይ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም ካለፈው ዓመት የ15 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ገልጸዋል።
በ6 ወራት 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን አዲስ ደምበኞች የባንክ ደብተር መክፈታቸውን ጠቅሰው በአጠቃላይ ደምበኞቹም 38 ነጥብ 1 ሚሊዮን ደርሷል ብለዋል።
በግማሽ ዓመቱ 55 ቅርንጫፎች የተከፈቱ ሲሆን የባንኩ ቅርንጫፎች 1879 ደርሷል።
የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 1 ነጥብ 123 ቲሪሊየን ብር መድረሱን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።