በ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የተገነባው ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እና ተርሚናል ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
በ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የተገነባው ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እና ተርሚናል ተመረቀ
ድሬ (ኢዜአ) ጥር 25/2015 በ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የተገነባው የድሬደዋ ደረቅ ወደብ እና ተረሚናል ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
የደረቅ ወደብ እና ተርሚናሉ የአገሪቱን የገቢ እና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴዎች በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ለሁለንተናዊ የምጣኔ ሃብት ዕድገትና የውጭ ምንዛሬ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።
የድሬደዋ ወደብ እና ተርሚናል በ34 ነጥብ 1ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ባለሶስት ወለል የቢሮ ህንፃ፣መጋዘን፣የኮንቴይነር ተርሚናልና 10 ሄክታር የውስጥ ለውስጥ የኮንክሪት መንገድ አለው።
በተጨማሪም በአንድ ጊዜ 140 መኪናዎች ማቆም የሚያስችል የተገነባ ቦታ ሁለት የዕቃ ማስቀመጫ መጋዘን እንዲሁም ወደቡን ከኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር የሚያገናኝ የባቡር ሃዲድ የተሰራለት መሆኑ ታውቋል።
በዛሬው እለት በመካሄድ ላይ በሚገኘው ምረቃ ላይ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አዲስ ብራንድ ይፋ ተደርጓል።