ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ

122

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 24/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በመሠረተ ልማት ትብብር፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን በማሳደግ እንዲሁም በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በሶማሊያ ከተካሄደው ቀጣናዊ የፀረ ሽብር ውይይት መድረክ ጎን ለጎን ከኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በመሠረተ ልማት ትብብር፣ በንግድና ኢንቨስትመንትን በማሳደግ እንዲሁም በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ስለሚኖር የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መክረናል" ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም