የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የውጭ ምንዛሬ መላኪያ አገልግሎትን በይፋ አስጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የውጭ ምንዛሬ መላኪያ አገልግሎትን በይፋ አስጀመረ
አዲስ አበባ(ኢዜአ) ጥር 22/2015 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮ ዳይሬክት' የተሰኘ ዲጂታል የውጭ ምንዛሬ መላኪያ አገልግሎትን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።
ካናዳ ፣ እስራኤል፣ አሜሪካ እና ጣሊያን አገልግሎቱ ከሚሰጥባቸው አገራት መካከል ይጠቀሳሉ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፤ አገልግሎቱ መጀመሩ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ለመላክ የሚወስድባቸውን ጊዜ፣ ገንዘብ ለመላክ የሚያወጡትን ገንዘብ እና ሕገ ወጥ የውጭ ገንዘብ ምንዛሬን ለመቀነስ ያግዛል ብለዋል።
ገንዘብ ተቀባይ ለሆኑ ሰዎችም ቀልጣፋ አገልግሎትን ለማግኘት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።