የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል በዲላ ከተማ እየተከበረ ነው

595

ዲላ (ኢዜአ) ጥር 20/2015 የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል በዲላ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የፌዴራልና የክልሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች ጨምሮ የዞኑ ነዋሪዎች ታድመዋል።

የዘንድሮው የዳራሮ በዓል አከባበር የጌዴኦ ባህላዊ የባሌ አስተዳደር በሚታወቅበት እሴቱ መሰረት ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሂደት የገዳ ሽግግር በተደረገበት ማግስት የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል።

ላለፉት 10 ቀናት በወረዳ ደረጃ ሲከበር የቆየው የዘመን መለወጫ በዓል ዛሬ ይጠናቀቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም