የ12ተኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የ12ተኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
የ2014 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ተኛ ክፍል) ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡
ተፈታኞች ከዛሬ ጥር18 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ፡-
• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝገባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ጉጹ ባሰፈረው መልእክት ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ እንዲጠቀሙም አስታውቋል፡፡
ተፈታኞች ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት ራሳቸውን እንዲጠብቁም ተመላክቷል፡፡