ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አደረጃጀቶች ያከናወኗቸው ተግባራትን የሚያስተዋውቅ መጽሐፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ (ኢዜአ)ጥር 18/2015 የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አደረጃጀቶች ያከናወኗቸው ተግባራትን የሚያስተዋውቅ መጽሐፍ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ ተመርቆ ይፋ ተደርጓል።

መጽሐፉ በስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮ-ዳያስፖራ የእውቅና መርሀግብር ላይ ይፋ ተደርጓል።

በመፅሐፉ ላይ 200 የሚሆኑ የዳያስፖራ አደረጃጀቶች ፕሮፋይል የተካተተበት መሆኑ ተመላክቷል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በመጽሀፉ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

"ኢትዮጵያ ባለውለታዎቿን አትረሳም" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው መርሀግብር 52 የዳያስፖራ አደረጃጀቶች በተለያዩ ዘርፎች ለሀገራቸው ባደረጉት አስተዋፆ ከክብር እንግዶች እውቅና እየተሰጣቸው ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም