የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በስድስት ወራት 19 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በስድስት ወራት 19 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 17/2015 የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በስድስት ወራት 19 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት አፈጻጸም አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሮባ መገርሳ በሰጡት መግለጫ ባለፉት ስድሰት ወራት 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቶን የኦፕሬሽን አገልግሎት መስጠቱን ገልጸዋል።
በተጨማሪም 312ሺህ ቶን ብትን እንዲሁም 4ሺ 500 በኮንቴይነር የታሸገ ጭነት መጓጓዙ ተናግረዋል።
በኮንቴይነር ከተጓጓዙት ጭነቶች መካከለ 3 ሺህ 79 በአገር ውስጥ መታሸጉንም ጠቁመዋል።
በዚህም ድርጅቱ በስድስት ወራቱ 19 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ነው የገለጹት፡፡
ተቋሙ በስድስት ወራቱ ከራሱ ፋይናንስ 185 ከባድ ተሽከርካሪዎችን መግዛቱን ገልፀው፤ በጅቡቲ እየተገጣጠሙ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ተቋሙ ተጨማሪ መርከቦችን የመግዛት እንቅስቃሴ እንደጀመረ ያስታወቁት ዋና ስራ አስፈፃሚው የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የንግድ መቀዛቀዝ ችግሮች እንዳጋጠመውም አንስተዋል፡፡