በአፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራ ልዑክ ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ቤቶችን ለማስረከብ ጅግጅጋ ገባ - ኢዜአ አማርኛ
በአፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራ ልዑክ ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ቤቶችን ለማስረከብ ጅግጅጋ ገባ
ጅግጅጋ (ኢዜአ) ጥር 17/2015 በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራ የምክር ቤት እና የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ቤቶችን ለማስረከብ ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።
ለአፈ ጉባኤውና አመራሮቹ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ አቀባበል አድርገዋል።
አፈ-ጉባኤው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመቀናጀት በጅግጅጋ ከተማ ለአቅመ ደካሞች እድሳትና ጥገና የተደረገላቸውን 31 መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች እንደሚያስተላልፉ ተመላክቷል።
ከሶማሌ ክልል መንግስት ጋር በመቀናጀት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ለሁሉም ህብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ በጅግጅጋ ከተማ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ምቹ መኖሪያ እንዲያገኙ የተሰራ ስራ መሆኑም ተጠቅሷል።
በበጎ ፍቃድ ስራው ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ተጠሪ ተቋማት በሆኑ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ ፣የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መሆኑም ተመልክቷል።