ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከሚገኙ የሀይማኖት አባቶች፣ ሲቪል ማህበራት፣ የአገር ሽማግሌዎች እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ ጥር 15/2015 /ኢዜአ/ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከሚገኙ የሀይማኖት አባቶች፣ ሲቪል ማህበራት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው።

የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ በኮሚሽኑ እስካሁን የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በውይይቱ መክፈቻ ላይ አብራርተዋል።

በውይይት መድረኩ የሀገራዊ ምክክር ጽንሰ ሀሳብ፣ ስለ አገራዊ ምክክር አስፈላጊነትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ገለጻ ተደርጓል።

በቀረበው ገለጻ ላይ የውይይቱ ተሳታፊዎች ውይይቶችን በማድረግ ቀጣይ በአገራዊ ምክክር ላይ በሚኖራቸው ሚና አቅጣጫ ያስቀሞጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘላቂ ሰላም ለማስፈን፣ ጠንካራና ቅቡልነት ላለው አገረ መንግስት ግንባታ ሂደት መደላድል ለመፍጠር አገራዊ ምክክር ማካሄድ ካስፈለገበት ውስጥ ይጠቀሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም