ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለቻይና ህዝብ አዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 14/2015 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለቻይና ሕዝብ አዲስ አመት የደስታና የብልጽግና ይሁንላችሁ ሲሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

May be an image of text that says '2023 Chinese New Year'

በመልዕክታቸውም የኢትዮጵያ እና ቻይና የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያድግበት አመት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ።

"አዲሱ ዓመት በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መካከል ጥንካሬና ቁርጠኝነት ይበልጥ ጎልቶ የሚታይበት እንዲሆን እመኛለሁ" ሲሉም መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም