ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት የአየር ሃይልና የሜካናይዝድ የጥምር ጦር ወታደራዊ ትሪኢትን ተመለከቱ

አዲስ አበባ ጥር 13/2015 /ኢዜአ/ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በመገኘት በአየር ሃይልና በሜካናይዝድ ተቀናጅቶ የተካሄደውን የጥምር ጦር ወታደራዊ ትሪኢት ተመልከቱ።

አየር ሃይልና ሜካናይዝድን በማዘመን ውጊያን በዘመናዊ የጦር መሳሪያና በውስን የሰው ሀይል የመጨረሰ አቅም እየተገነባ እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ተናግረዋል።

May be an image of 1 person, jeep, road and sky

በመርሐ ግብሩ ላይ የመከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ምክትል ኤታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ፣ የአየር ኃይል አዛዥ ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የፌደራል ፖሊሲ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤልና ሌሎችም የመከላከያ ከፍተኛ አዛዦችና መኮንኖች ተገኝተዋል።

በመቀጠልም በቢሾፍቱ አየር ኃይል ዋና መምሪያ ተገኝተው በዝግጁነት ላይ የሚደረጉትን ማሻሻያዎች ጎብኝተዋል::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም